DJ Jop V.#22 - Best of Elias melka ኤሊያስ መልካ Music nonstop Mix (teddy afro,gosaye, etc)
1,808,836
Published 2019-10-10
🏦 CBE -- 1000236801261
📲 Tele Birr - 09 11 53 43 99
የኤሊያስ መልካ ያቀናበራቸው ምርጥ ሙዚቃዎች ስብስብ
Mixed by DJ Jop Ethiopia
DJ Jop is a Multi-talented Club DJ, Wedding DJ, Mashup Artist and one of the Ethiopian Pioneer Video DJ (VJ)
For DJ Booking : 0911534399
Download The Audio from Telegram here -- t.me/DjJop
• DJ Jop Ethiopia #41 (ከ.ል.ብ) Quarantin...
New Nonstop mixxx
ሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ኤልያስ መልካ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው፡፡ ሙዚቃ የጀመረው በለጋ ዕድሜው ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡
ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ፣ ፒያኖና ክራር የተማረ ሲሆን፣ በመዲና፣ አፍሮ ሳውንድ፣ ዜማ ላስታስና ሌሎችም ባንዶች ከሠራ በኋላ፣ በራሱ ስቱዲዮ (በገና ስቱዲዮ) ወደ መሥራት ተሸጋገረ፡፡
ከአንጋፋዎቹ ድምፃውያን መሐሙድ አህመድ፣ ዓለማየሁ እሸቴና አስቴር አወቀ አንስቶ በበርካታ ሙዚቀኞች አልበም ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስመ ጥር ከሆኑ ሙዚቀኞች አንዱ ኤልያስ፣ ከሠራቸው አልበሞች የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ እዮብ መኮንን፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካያ በኃይሉ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አብነት አጎናፍርና ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪ የጌቴ አንለይ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱና ዘለቀ ገሠሠ አልበሞችም ይገኙበታል፡፡
እሱ፣ ኃይሌ ሩትስ፣ ዮሐንስ በቀለ (ጆኒ ራጋ) እና ሌሎች ባለሙያዎች በጥምረት በሚሠሩበት አውታር መልቲሚዲያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር አዲስ የሙዚቃ ገበያ መገበያያ ሥርዓት አስተዋወቋል ፡፡ ይህ በኮፒ ራይት መብት ጥሰት ሳቢያ የተመሰቃቀለውን ሙዚቃ ይለውጣል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል፡፡
ኤልያስ መልካ እንደ ብዙ ሰው ነው
.
1 ጊታሪስት (ሊድ)
2 ቤዚስት
3 ፒያኒስት
4 ድራመር
5 ሳክስፎኒስት
6 ኮንዳክተር
7 ገጣሚ (የረቀቀ)
8 ዜማ ደራሲ
9 አቀናባሪ
10 ፕሮድዩሰር ይሄን ሁሉ መሆን ለአንድ ሰው ከባድ ነው ።
#ኤለያስ_መልካ ነፍስህን በገነት ያኑራት. ላበረከትክልን ስራዎች እናመሰግናለን
#DJ_Jop_Mix
All Comments (21)
-
😭😭😭😭😭😭😭 ባየውት ቁጥር ነው ማለቅሰው 💔 ሳይሞት ማንገስ ነበረብን ለስራው መመስገን ነበረበት እንደሻማ ቀለጠ የኔ ቆንጆ ውበቱ እስኪጠፋ 😭 ነብስህን በገነት ያኑራት ሁሌም አንረሳህም ❤
-
የኤልያስ ሞት ዛሬም2013 ያልወጣለት ማነው ሁሌም ስራወችህን ሰሠማ ፌቴ በእንባ ይታጠባል ነፍስ ይማር።
-
የሰዉ ልጅ ሁሌም ወደ ሞት ነዉ:ግን የማይሞት ስራ ሰርቶ መሞት ሞትን ማሸነፍ ነዉ:#ኤልያስ ልጅነታችንን አሳምረክልናል ሁሌም በልባችን ነህ!!
-
ኤልያስ መልካ ሙዚቀኛ አይደለም ወይም የሙዚቃ አቀናባሪ አይደለም....ራሱ ሙዚቃ ነው💚💛❤️መቼም የማይተካ
-
ኤልያስ መልካ ስለሌሎች ማበብ አራሱን ያከሰመ ፤ ለዚህ ስግብግብ አለም እና ራስ ወዳድ ትዉልድ ያልተገባ ድንቅ ሰዉ ፻
-
እኛ ኢትዮጵያን ዱሮም የአገር ባላዉለታ ሰዉ ታሞ ታቻግሮ አንጣይቅም ከሞቴ ቦኃላ ነዉ የምቆጨን ይህ ወርቅ የመሰለ ልጂ አፋር መሰሎ ምን ሆንክ ያለዉ የለም በሕይወት እያል ሕይት ታርክ ብዛከር ጥሩ ነበር ምንም ብታወሩ እሱ አሁን አይሰማም ወዴ ፊጣር ሄደዋል ነፋሳ ይመር
-
የሆዴ መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት😭😭😭😭😭ኤልያስ ስራዎችህ ከመቃብር በላይ ይኖራሉ 😭😭🙏
-
ይሄን ሁላ ወርቅ ስራ ሰርቶ ማለፍ የማይታመን ጀግንነት ነው። የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባለውለታ ነህ ኤልያስ 🙏
-
ይገርማል የማዉቃቸው ምርጥ ሙዚቃዎች ሁሉ የኤልያስ ናቸው ነፍሱን በገነት ያኑረው
-
ኤላ የማውቃቸው ስራዎችህ ሁሉ አሁን ከሚሠሩት ሙዚቃዎች 100% የተሻሉ ናቸው ብትኖርና ብታግዘኝ ብዬ እመኝ ነበር ግን ፈጣሪ በጊዜው ነብስህን ወስዷል ፈጣሪ ከደጋጎቹ ከመልካሞቹ ወንድም እህቶቼ ተርታ ያስቀምጥህ
-
ጀግና ይችላል
-
ለነዚህ ካሃድያን ዘፋኞች ብለህ እንደ ሸማ ቀለጥቅ ያንተ ስራዎች ሁሌ ህያው ናቸው Rip Legend
-
ኤልያስ ነብስህን በገነት ያኑራት. ዲጄው wow
-
ልጅነቴን የሚያሰታውሱ ዘፈኖች።ኤልዬ መለየትህን መቀበል ከበደኝ በስጋ የተወልድከኝ ያህል ይሄው ሳምንት ሙሉ አለቅሳለሁ ምርጥ ሰው❤❤❤
-
ኤሊ የድንግል ልጅ ጌታ መድኃኒዓለም ነብስህን በገነት ያኑራት!!!
-
ኧረ ኡኡኡኡኡኡ ....ዘንድሮስ ተቃጠልኩ ። ኤልያስዬ የኔ ጌታ ምነው ባላወኩህ ወይም ምነው አንተ ኖረህ እኔ ባንተ ፈንታ ህመምህን ታምሜ ሞትህን ብሞትልህ ።መታመምህን ሣልሠማ ሳላውቅ ማለፍህን ስሠማ ተንገበገብኩ ,ተቃጠልኩ ። የኔ ጌታ ፈጣሪ ነብስህን በገነት ያኑራት ሌላማ ምን እላለው .......💔😥😥😥😥😥😥
-
ለእነ ሙላቱ አስጣቄ ማሽቃበጥ የሙዚቃ አዋቂዎች ይመስለናል: ግን ለእኔ እንደ ኤልያስ እና አበጋዝ ሾታ የመሰለን የሙዚቃ አቀናባሪ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አላየሁም❤❤❤❤❤
-
ኤልያሥየ ሞት በሁላችንም ዘድየማይቀር ነው ሁላችንም ወዳተ ነን ሥራወችህ ግን ህያዉ ሁኖ ለዘላለም ይኖራል ነፉሥህን ባፀደ ገነት ያኑራት
-
ኤልያስ የሚገርም ነው ሰው ለካ የዚህን ያህል አቅም አለው የሚያስብል ነው እግዚአብሔር ነብስህን ከመልካሞቹ ጎን ያርገው
-
ሙዚቃን በልዩ ሁኔታ እንድወድ ያስገደደኝ ፡የልጅነት ድንቅ ዘመነኔን በሰራቻው ድነቅ ሙዚቃዎች ያሳመረልኝ ዘግይቶ አልገባኝም። ሙዚቃዎችን ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ ቢቱ ሲጀምር ገና የኤልያስ ድንቅ አእምሮና የጣቶቹ አሻራዎች እንዳሉበት ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ። ዘመኑ አጭር ቢሆኑም መስራት ከአለበት በላይ የሰራ ድንቅ ሀገሬ ካጣቻቸው ድንቅ ሰዎች በመጀመሪያው ተርታ የሚሰለፍ የዘመኔ ህይወት አጣፋጭ ሰው ነው ።